ማሊያዊው የፊት እና የመስመር አጥቂ አማራ ማሌ አዲሱ ፈረሰኛ ለመሆን ተቃርቧል።
በአሁኑ ሰዓት በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በሙከራ ላይ ከሚገኙት 3 ተጨዋቾች መካከል የማሊ ዜግነት ያለው አማራ ማሌ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኞችን ማሳመን እንደቻለ የፈረሰኞቹ ገጽ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አሳውቀውናል። ይህ የፊት እና የመስመር አጥቂ ተጨዋች በልምምድ ሜዳ እያሳየ ካለው ብቃት መነሻነት የክለቡ አሰልጣኞች በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ተጨዋቹ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይጠቅማል ብለው በማመናቸው በቀጣይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ተጨዋች መጪውን አዲስ አመት በማስመልከት በቀጣይ ቀናት ወደ ማሊ የሚጓዝ ሲሆን አዲስ አመትን በአገሩ አሳልፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ያሳያል፡፡ አማራ ማሌ በማሊ እግርኳስ ክለብ ታሪክ ታላላቅ ስም ባላቸው ክለቦች ውስጥ ያለፈ ተጨዋች ነው። በአሁኑ ወቅት በማሊ ታላቅ ክለብ የሆነው የስታድ ማሊ ክለብ ተጨዋች ሲሆን 1 ሜትር ከ 82 ሳንቲሜትር ይረዝማል። ይህ ተጨዋች በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ ታህሳስ 5 ቀን 1982 እንደተወለደ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ተጨዋቹ 25 ዓመቱ ሲሆን በሁለቱም እግሮቹ ኳስ መጫወት የሚችል ተጨዋች ነው ፡፡ በ አ ከ 2009-2012 የማሊ ክለብ ለሆነው ባማኮ፣ 2013-2015 ለጆሊባ እንዲሁም በ 2016 ወደ ጊኒ ተጉዞ...