የቀጥታ ስርጭት፦ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ



(በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚካሄደውን ይህ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታ ዋና ዋና እንቅስቃሴ በዚህ ሊንክ ላይ በኤዲት የምናካትት ይሆናል። የፈረሰኞቹ ገጽ ተከታታዮች ይህንን ሊንክ ሪፍሬሽ በማድረግ የጨዋታውን አበይት የየደቂቃ እንቅስቃሴዎች ማግኘት የምትችሉ ይሆናል።)

********
አጠቃላይ ውጤት:— ወልዋሎ አዲግራት የኒቨርስቲ 0-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ
********

ጨዋታውን ለመጀመር ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተዋል።

1‘ ጨዋታው በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኳስ ጀማሪነት ተጀምሯል።

2‘ የቀድሞ የፈረሰኞቹ የግራ መስመር አጥቂ ፕሪንስ ሰርቪንዮ የቀድሞ ክለቡን እየገጠመ ይገኛል።

4‘ ክለባቸውን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ በተለያዩ የትራንስፓርት አማራጮች የተጓዙት የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አጠራር በካታንጋ አከባቢ በመቀመጥ ክለባቸውን እያበረታቱ ይገኛሉ።

6‘ ምንተስኖት አዳነ በዛሬው ጨዋታ ፈረሰኞቹን በአንበልነት እየመራ ወደ ሜዳ ገብቷል።

8‘ ፕሪንስ ሰርቪኒዮ በመልሶ ማጥቃት ያገኘውን ኳስ በቀጥታ ወደ ጎል ቢመታውም በሮበርት ኦዶንካራ በቀላሉ ተይዟል።

10‘ አቡበከር ሳኒ ከመስመር ወደ ሳጥን ያሻገረውን ጥሩ ኳስ ምንተስኖት አዳነ ወደ ጎል ቢመታውም በግብ ጠባቂው ተይዞበታል።

12‘ ምንም እንኳን የጨዋታው ሜዳ ለጨዋታ አመቺ ባይሆንም ፈረሰኞቹ ኳስን ተቆጣጥረው ወደ ግብ ክልል ለመድረስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

14‘ አበባው ቡጣቆ ከሜዳው በስተግራ የተገኘውን ቅጣት ምት ወደ ጎል አሻምቶ ሳላሃዲን በርጌቾ በጭንቅላቱ ለመግጨት ቢሞክርም የመሃል ዳኛው ግብ ጠባቂው ላይ ጥፋት ተሰርቷል ብለው ጨዋታው በቅጣት ምት ቀጥሏል።

17‘ ጋዲሳ መብራቴ በተደጋጋሚ ተከላካዮችን እያለፈ ወደ ፊት ለመሄድ ቢሞክርም የመጨረሻ ኳሶቹ የተሳኩ አይደሉም።

20‘ ጨዋታው ይህ ነው የሚባል የግብ ማግባት ሙከራ እያስተናገደ አይገኝም ሁለቱም ቡድኖች በመሃል ሜዳ ለይ ያተኮረ እንቅስቃሴ እያከናወኑ ይገኛሉ።

22‘ አበባው ቡጣቆ ከቅጣት ምት ወደ ሳጥን ያሻማው ጥሩ ኳስ በግብ ጠባቂው ተመልሷል።

23‘ ፈረሰኞቹ በጨዋተው ላይ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ይገኘሉ።

25‘ ፒሪንስ ሰርቪኒዮ ከግራ መስመር ከባድ ኳስ መትቶ በሮበርት ብቃት ኳሱ ተመልሷል።

29‘ ወልዋሎዎች ከመሃዘን ምት ያገኙትን ኳስ ወደ ውጭ አሻምተውት በቀጥታ ወደ ጎል የመቱት ኳስ ለጥቂት ወደ ውጭ ወጥቷል።

31‘ ወልዋሎዎች በመጠኑ የጨዋታ ብልጫን እየወሰዱ ይገኛሉ።

33‘ አቡበከር ሳኒ ከተከላካዮች ጋር ተጋፍቶ ጎል አስቆጥሮ የነበረ ቢሆንም ጥፋት በመስራቱ ጨዋታው በቅጣት ምት ቀጥሏል።

34‘ ጋዲሳ መብራቴ ከሜዳው በስተቀኝ ወደ ግብ ክልል እያጠበበ ገብቶ የመታው ጥሩ ኳስ በግብ ጠባቂው ተመልሶ የመሃዘን ምት ሆኗል።

38‘ የወልዋሎ አዲግራት ተጨዋች ተጎድቶ በመውደቁ የጨዋታው እንቅስቃሴ ተቋርጧል።

39‘ ወልዋሎዎች ከርቀት ወደ ግብ አክርረው የመቱት ኳስ የግቡን አግዳሚ ገጭታ ተመልሳለች። የተመለሰችውን ኳስ በድጋሚ ብቻቸውን ቢያገኙትም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

41‘ ፈረሰኞቹ ምንም እንኳን ኳስን ተቆጣጥረው ለመጫወት ጥረት እያደረጉ ቢገኙም አሁንም የሜዳው ሶስተኛው ክፍል ላይ የሚያደርጓቸው ቅብብሎች የተሳኩ አይደሉም።

44‘ ወልዋሎዎች ግልፅ የማግባት እድል አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። ሮበርት ኦዶንካራ በድንቅ ብቃት ኳሱን አድኖታል።

የጨዋታው ግማሽ ክፍለጊዜ 0—0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ ኳስ ጀማሪነት ተጀምሯል።

46‘ የተጨዋች ቅያሪ ጋዲሳ መብራቴ ወጥቶ አዳነ ግርማ ወደ ሜዳ ገብቷል።

46‘ አዳነ ግርማ ከርቀት የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ወደ ጎል ቢመታውም በግብ ጠባቂው ተመልሷል። ኳሱ ሲመለስ በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው አቡበከር ሳኒ ኳሱን ሳይደርስባት በተከላካይ ተመልሶ የመሃዘን ምት ሆኗል።

48‘ የተጨዋች ቅያሪውን ተከትሎ አደነ ግርማ የቡድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሲሆን ኢብራሂም ፎፎና የቀኝ መስመር አጥቂ ሆኗል። በተጨማሪም አዳነ ግርማ የአንበልነት ማዕረጉን ከምንተስኖት አዳነ ተቀብሎ ቡድኑን በአንበለወነት እየመራ ይገኛል።

55‘ ወልዋሎዎች አልፎ አልፎ ከመስመር ወደ ሳጥን የሚያሻሟቸው ኳሶች የፈረሰኞቹን ተከላካዮች ጫና ውስጥ እየከተታቸው ይገኛል።

57‘ ፈረሰኞቹ ከእረፍት መልስ በመጠኑ ወደ ኃላ አፈግፍገው እየተጫወቱ ይገኛሉ ይህም በተጋጣሚያቸው ጫና እንዲፈጠርባቸው እያደረገ ይገኛል።

59‘ ፈረሰኞቹ በያዝነው የውድድር አመት ይህ ሁለተኛው የክልል ጨዋተቸው ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ሲዳማ ለይ አድርገው ሲዳማ ቡናን 1—0 አሸንፈው መመለሳቸው ይታወሳል።

62‘ ወልዋሎዎች በድጋሚ ግልፅ የማግባት እድልን አግኝተው ሳይጠቀሙበት ኳሱ ወደ ውጭ ወጥቷል።

64‘ ወልዋሎዎች ከእረፍት መልስ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ ወደ ግብ ክልል እየደረሱ እና ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ።

66‘ ኢብራሂም ፎፎና ከአዳነ ግርማ ጋር አንድ ሁለት ተቀባብለው ያገኘውን ኳስ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

68‘ ወልዋሎዎች ከግቡ ቅርብ ርቀት ያገኙትን ቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ጎል ቢመቱትም ኳሱ ከግቡ ርቀት ወደ ውጭ ወጥታለች።

70‘ አብዱል ከሪም ኒኪማ በመልሶ ማጥቃት ይዞት የገባውን ኳስ ወደ ሳጥን ቢያሻማውም በቦታው ተጨዋች ባለመኖሩ ኳሱ ወደ ውጭ ወጥቷል።

72‘ ወልዋሎዎች ከ16:50 ጠርዝ ላይ ያገኙትን ቅጣት ምት ወደ ግብ ቢመቱትም ኳሱ በተከላካዮች ተመልሷል።

73‘ ወልዋሎዎች በድጋሚ በፈረሰኞቹ የግብ ክልል ውስጥ ጥሩ ኳስ አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

76‘ ፈረሰኞቹ ከእረፍት መልስ ኳስን ተቆጣጥሮ ወደ ግብ ክልል ከመድረስ ይልቅ በረዣዥም ኳሶች ግብ ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

77‘ የተጨዋች ቅያሪ ኢብራሂም ፎፎና ወጥቶ ሲዲ መሃመድ ኬታ ወደ ሜዳ ገብቷል።

79‘ ከተጨዋች ቅያሪው በኃላ ኬታ የፊት መስመር አጥቂ ሲሆን አዳነ ግርማ የአጥቂ አማከይ ሆኗል አብዱል ከሪም ኒኪመ የመስመር አጥቂነት ሚና ተሰጥቶታል።

81‘ የወልዋሎ አዲግራት ተጨዋች ተጎድቶ በመውደቁ የጨዋታው እንቅስቃሴ ተቋርጧል።

86‘ የተጨዋች ቅያሪ አብዱልከሪም ኒኪማ ወጥቶ ተስፋዬ በቀለ ወደ ሜዳ ገብቷል።

ተጨማሪ ደቂቃ 3‘ ደቂቃ

90+1‘ ፈረሰኞቹ ወደ ኃላ አፈግፍገው በመጫወት ይገኛሉ።

90+2‘ ወልዋሎዎች ያገኙትን የመሃዘን ምት ወደ ጎል ቢያሻሙትም ኳሱ ወደ ውጭ ወጥቷል።

የጨዋታው ሙሉ ክፍለጊዜ 0—0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

****************

የቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ቀዳሚ ተሰላፊዎች፦
ግብ ጠባቂ – ሮበርት ኦዶንኮራ
ተከላካዮች – አበባው ቡጣቆ፣ አስቻለው ታመነ፣ ሳላሃዲን በርጌቾ፣ አብዱልከሪም መሀመድ
አማካዮች– አብዱልከሪም ኒኪማ፣ ሙሉአለም መስፍን፣ ምንተስኖት አዳነ
አጥቂ —አቡበከር ሳኒ፣ኢብራሂም ፎፎና፣ጋዲሳ መብራቴ

********
ተጠባባቂዎች፦
-ዘሪሁን ታደለ
-አሉላ ግርማ
-ደጉ ደበበ
-በሃይሉ አሰፋ
-ተስፋዬ በቀለ
-አዳነ ግርማ
-መሃመድ ሲዲ ኬታ

Comments

Popular posts from this blog

ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!

በሚዲያ አጠቃቀም የኋልዮሽ ጉዞ ላይ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ!

በፖለቲካ የተዋጠው፣ የፖለቲከኞች እጅ የተጫነው እግርኳሳችን! - በፈረሰኞቹ ገጽ