3 የምዕራብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በሙከራ ላይ ይገኛሉ፡፡


ቅዱስ ጊዮርጊስ ለተለያዩ የውጭ አገር ዜግነት ላላቸው ተጨዋቾች የሙከራ ዕድል እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ከተለየዩ ወኪሎች ጋር ግንኙነቶችን በመፍጠር ተጨዋቾች የሙከራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት የተለመደ አሰራር ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሙከራ ጊዜያቸውን በተሳካ መንገድ በማለፍ ለክለቡ የፈረሙ ተጨዋቾች እንዳሉ ሁሉ ቁጥራቸው የበዛ የውጭ አገር ተጨዋቾች በሙከራ ጊዜያቸው አሰልጣኞቹን ማሳመን ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ አገራቸው አሊያም በአገር ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክለቦች እንዳቀኑ ይታወቃል፡፡



በአሁኑ ሰዓት የሙከራ ዕድል የሰጣቸው 3 ተጨዋች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተጨዋቾች ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አዲግራት በማቅናቱ ምክንያት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከ20 ዓመት በታች ስብስብ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ከናይጄሪያ፣ ጋና እና ማሊ ሀገራት የመጡ መሆኑን የፈረሰኞቹ ገጽ ምንጮች አረጋግጠውልናል፡፡


በዛሬው የልምምድ መርኃ ግብር ላይ ተገኝተን መመልከት እንደቻልነው እነዚህ ተጨዋቾች ከዋናው ቡድን ጋር ተቀላቅለው ልምምድ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ ከቡድኑ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ተገምግመው እንዲሁም አሰልጣኞቹን ማሳመን ከቻሉ በ2ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንዲሁም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያ የሚታዩ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው አሰልጣኞቹን ማሳመን ካልቻሉ የሙከራ ጊዜያቸው ማብቃቱን ተከትሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚለያዩ ይሆናል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ፡- ወልድያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ

ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!