የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝማሬዎችን በቀጭኑ ሽቦ!
እኛ ቅዱስ ጊዮርጊሳውያን ክለባችንን ባገኘበው መንገድ ሁሉ ለማስተዋወቅ አንሰንፍም፡፡ ስለ ክለባችን ለመናገር አንቦዝንም፡፡ የዕለት ተዕለት ጉዟችን ውስጥ ክለባችን አለ፡፡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡
ዛሬ ጊዮርጊስን የምናስተዋውቅበት አማራጮችን በአንድ አሳድገናል፡፡ ስለ እግርኳስ ለሚያውቁት ብቻ ሳይሆን ስለ እግርኳስ ለማያውቁት በዙሪያችን ላሉ ሁሉ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የምናሳውቅበት መንገድ ተመቻችቶልናል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝማሬዎችን ቤተሰቦቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ የሥራ ባልደረቦቻችን እንዲያወቁና ዝማሬያችንን እንዲሰሙ የማድረጊያው መንገድ አግኝተናል፡፡ ከአፋችን የማይጠፉ ዝማሬዎቻችን ለስልኮቻችን ተዘጋጅተውልናል፡፡
ከዛሬ አንስቶ እኛ ብቻ ሳንሆን ስልኮቻችንም ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይናገራሉ፤ ቅዱስ ጊዮርጊሳዊ መሆናችንን ይሰብካሉ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ማራኪ ዝማሬዎች ይላበሳሉ፡፡ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የሚደወሉ ጥሪዎች በሙሉ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጉዞ፣ ውጣ ውረድ፣ ድል፣ ስኬት፣ ቤተሰባዊነት እና መሰል ኹነቶችን ለመስማት ይገደዳሉ፡፡
በቅድሚያ በሞባይል የስልክ የጽሑፍ መልዕከት መላኪያ ስፍራ ውስጥ እንግባ፡፡ በመቀጠል 822 ላይ “A” በማለት መልዕክት እንላክ፡፡ በመቀጠል ከ822 የCRBTተጠቃሚ መሆን መጀመራችንን የሚገልጽ የጽሑፍ መልዕክት ይደርሰናል፡፡ በመቀጠል የጥሪ ማሳመሪያ እንዲሆን የወደድነውን ዝማሬ ኮድ ብቻ ወደ 822 እንላክ፡፡ ከዚያም ከ822 የመረጥነው ዝማሬ የጥሪ ማሳመሪያ እንደሆነ ማረጋገጫ ይደርሰናል፡፡ ይህ ካልተሳካ ግን በድጋሚ የወደድነውን ዝማሬ ኮድ ብቻ ወደ 822 ለመላክ እንሞክር፡፡ ከእነዚህ ቅጽበቶች አንስቶ ወደ ስልካችን የሚደወሉ ስልኮች በሙሉ በመረጥነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዝማሬ ይታጀባሉ፡፡
Comments
Post a Comment