ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!
ውድ የፈረሰኞቹ ገጽ ተከታታዮች ይህ ገጽ ለ 3 አመታት ለቀረቡ ጊዜያት ያህል ቅዱስ ጊዮርጊስን በተመለከተ ዘገባ ሲሰራ በደጋፊዎች መሃል የሚነሱ ግጭቶችን እምብዛም ሽፋን አይሰጥም ነበር። ምክንያቱም ግጭቶቹ እግርኳሳዊ በመሆናቸው እና በአገራችን ሜዳዎች የሚከሰቱ ግጭቶች የተለመዱ እና እግርኳሳዊ ፉክክሮች የሚያስነሳቸው በመሆናቸው ነበር። እንዲሁም የፈረሰኞቹ ገጽ በዳኛ ውሳኔ ላይ በፍፁም አስተያየት ሰጥቶ አያውቅም። በተጨማሪም በዳኛ ውሳኔ ላይ ግላዊ አሰተያየቶችን በገፃችን ላይ አቅርበን አናውቅም። ምክንያታችንም የዳኛ ስህተት የእግርኳስ የጨዋታ አካል በመሆኑ እንዲሁም ስህተቶች ያሉ እና የሚኖሩ በመሆናቸው ብቻ ነበር። ሆኖም በጅማ ስታዲየም የተከሰተው ፍፁም ከእግርኳስ መሰረታዊ መርህ ያፈነገጠ፣ በእግርኳስ ሜዳ ሊከሰት የማይገባው እና የፈረሰኞቹ ገጽ እንደ አንድ የስፖርቱ ባለድርሻ አካል የምናወግዘው በመሆኑ የተፈጠሩ ሁነቶችም አንድ ሁለት ብለን ልንናገር ወደድን። በጅማ ስታዲየም የመጀመሪያው ችግር የተከሰተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ወደ ጅማ ከተማ ሲደርሱ ነው። ደጋፊዎቹ በአውቶብሶቻቸው ላይ ሆነው እየዘመሩ ወደ ጅማ ከተማ ሲገቡ ከከተማው ነዋሪዎች የጠበቃቸው ነገር አስደንጋጭ ነበር። « አሸንፋችሁን ከዚህ ከተማ በሰላም እንወጣለን ብላችሁ ካሰባችሁ የዋሆች ናችሁ » የሚሉ ድምፆች በርካቶች ናቸው። ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ከተጓዙ አውቶብሶች መካከል በ 1 አውቶብስ ላይ ድንጋይ ሲወረወር የፈረ...