Posts

Showing posts from April, 2018

It's Match Day!

Image
In Ethiopia, where everything is a challenge, among few things that remained real is St George. St George did not become a history. It did not stop on "it was". It is only our St George that is still on a route it created yesterday before ages. Many clubs could not stand founded later than St George and on better times.  We have a club founded at Arada by youngsters who were ahead of time.   When football was new to Ethiopia, it was us who made the Ethiopian football carrying goal posts from fields to fields, making lines with chalks, wearing sweater as jersey and paid popcorn as a signing fee of players. We thought football's ''A B C D'' spending from our pockets. When Blacks and Whites were different teams because of color, we stood for the impossible, humanity. Using football for freedom, we waved the Green-Yellow-Red flag on Addis Ababa before Emperor HaileSilassie the First and declared our freedom. We are champions of Ethiopian Pre...

የፈረሰኞቹ ገጽ ‏- ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው!

Image
መውጣትና መውረድ ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ ካልከሸፉ እውነታዎች ውስጥ አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪክ ሆኖ አልቀረም። «ነበር» በሚባል ቃል ያላበቃ ክለብ ነው። ከዘመናት በፊት፣ ከዘመናት በኋላ፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ ባሰመረው መስመር እየተጓዘ የሚገኘው የእኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ በኋላ ተመስርተው ያልፀኑ፣ በተሻለ ዘመን ተነስተው በእግራቸው ያልቆሙ ክለቦች እልፍ ናቸው። ዘመናቸውን የቀደሙ፣ ነገን ቀድመው በተረዱ ወጣቶች አራዳ ላይ በአራዳዎች የተመሰረተ ክለብ አለን። እግር ኳስ በኢትዮጵያ እንግዳ በነበረበት ጊዜ ከሜዳ ሜዳ አንግል እየተሸከምን፣ በኖራ መስመር ሰርተን፣ ሹራብ እንደ ማልያ ለብሰን፣ ተጨዋቾችን ለማስፈረሚያ ቆሎን እንደ ክፍያ ሰጥተን የኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክን ጠፍጥፈን የሰራን እኛ ነን። ከኪሳችን ገንዘብ እያዋጣን የእግር ኳስን «ሀ፣ ሁ» ያስተማርን ቀዳሚዎች እኛ ነን። ነጭና ጥቁር በቀለማቸው ብቻ በተቦደኑት በዚያ ጊዜ የማይሞከረውን እንዲሆን በማድረግ በሰብአዊነት የቆምን እኛ ነን። እግር ኳስን ለሀገራዊ ነፃነት እንቅስቃሴ በማዋል ከንጉሥ ኃይለሥላሴ ቀድመን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን በአዲስ አበባ አውለብልበን ነፃነታችንን ያረጋገጥን እኛ ነን። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለ14 ጊዜ ዋንጫ ወስደናል። ውድድሩ እንደ አዲስ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለብቻችን በፍፁም የበላይነት የከበርን እኛ ብቻ ነን። ሀገራችንን በተደጋጋሚ በአፍሪካ መድረክ በመወከል ስማችንን በጉልህ የፃፍን፣ ለአራት ተከታታይ አመታት ማንንም ጣልቃ ሳናስገባ የሊጉን ዋንጫ ያነሳን እኛ ብቻ ነን። በሊጉ ውድድር ያለምንም ሽንፈት ዋንጫ አንስተን የማይቻለውን ችለን ያሳየን እኛ ብቻ ነን። የአዲስ አበባ ...