በሚዲያ አጠቃቀም የኋልዮሽ ጉዞ ላይ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ!
ቅዱስ ጊዮርጊስ በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ውጤት በማምጣት ጭምር እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ከአፍሪካ ታላላቅ ክለቦች ጋር ጨዋታዎችን ማድረግ ችለናል፡፡ ከታላላቅ ክለቦች ጋር ስንጫወት ከእግር ኳሱ ጎን ለጎን የምንቀስማቸው አስተዳደራዊ እና መሰል ተግባራት ሊኖሩ ይገባል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ ገብቶ ጨዋታዎችን ሲያደርግ የነበረው የሚዲያ አጠቃቀም ደካማ ነበር፡፡ ሆኖም የፈረሰኞቹ ገጽ በዚያ ወቅት አንድም ነገር ለመናገር አልወደድንም ነበር፡፡ ምክንያታችን የነበረው ለውድድሩ እንግዳ ከመሆን የመነጨ ነው በሚል ነበር፡፡ ይህ ከያዝነው ውድድር ዓመት አንስቶ ይስተካከላል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ ሆኖም ግምታችን ትክክል አልነበረም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬም በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ እጅግ ደካማ ክለብ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ምስረታ ከረጅም አመት በኋላ የተመሰረቱ ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ ሲንቀሳቀሱ እየታዘብን እንገኛለን፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ብዙም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ታሪክ የሌላቸው ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንደሚሻሉ እያየን ነው፡፡ ለዚህም ማሳያዎችን እንጥቀስ፡፡ 1. የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይፋዊ ድረ ገጽ! ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የራሱን ድረ ገጽ ከፍቶ መረጃዎችን ያስተላልፍ ነበር፡፡ ምንም እንኳ ድረ ገጹ ዘመናዊነት ያልተከተለ ቢሆንም ጥረቶቹ ግን የሚያበረታቱ ነበሩ፡፡ ይህ ድረ ገጽ አሁን ላይ አገልግሎት አይሰጥም፡፡ ከዓመታት በፊት የተሰጡትን መረጃዎች ይዞ ተቀምጧል፡፡ በአሁን ሰዓት የድረ ገጹ የደረጃ ሰንጠረዥ ማሳያ እያሳየው የሚገኘው የ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ...