የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ ሳላሃዲን ሰኢድ ወደ ልምምድ ተመለሰ!
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት አጥቂ ሳላሃዲን ሰኢድ ካለፈው የውድድር ዓመት ፍጻሜ አንስቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያ በውድድሮች ላይ ያልታየ ተጨዋች ነው፡፡ ሳላሃዲን በጉዳት ምክንያት የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ላይ ያልነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከጉዳት መልስ ከቡድኑ ጋር ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም በልምምድ ሜዳ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በድጋሚ ከቡድኑ ውጪ ለመሆን ተገዶ ነበር፡፡
የፈረሰኞቹ ገጽ በዛሬው የልምምድ መርኃ ግብር ላይ ተገኝቶ ለመመልከት እንደቻለው ይህ የፊት መስመር ተጨዋች ወደ ቀላል ልምምድ ተመልሷል፡፡ ሳላሃዲን ባለፉት ጊዜያት በጂምናዚየም ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዚህ ሰዓት በልምምድ ሜዳ ተገኝቶ በህክምና አካላት በመታገዝ ቀላል ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ቀላል ልምምድ ተጨዋቾች ከጉዳት ሲመለሱ የሚያደርጉት የሰውነት ማላቀቅ እና መጠነኛ ሩጫ ሲሆን በቀጣይ ወደ ሙሉ ልምምዶች ለመሸጋገር ለቀናት የሚካሄድ እንቅስቃሴ ነው፡፡
Comments
Post a Comment