የቡርኪና ፋሶ ተወላጅ የሆነው አብዱልከሪም ኒኪማ ወደ ልምምድ ተመልሷል፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ አማካይ ተጨዋች የሆነው አብዱልከሪም ኒኪማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባ ጅፋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት በህመም ምክንያት ከቡድኑ ውጪ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ፈረሰኛ ባጋጠመው ከባድ የጉንፋን ህመም ምክንያት ያለፉትን ቀናት በእረፍት አሳልፏል፡፡ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባ ጅፋር ያደረጉትን ጨዋታ ከተመልካች ጋር ሆኖ ለመከታተል ተገዶ ነበር፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባ ጅፋር ድል በኋላ የ1 ቀን እረፍት አድርጎ በዛሬው ዕለት ወደ ልምምድ ሲመለስ ይህ የቡርኪና ፋሶ ተወላጅ የሆነው ተጨዋች ወደ ቡድኑ ተቀላቅሏል፡፡ አብዱልከሪም ኒኪማ በዛሬው ዕለት ወደ ቡድኑ ከመመለሱ ጎን ለጎን በቀጣይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ9 ቀናት ውስጥ በሚያደርገው 3 ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጥር 4 ወደ ወልድያ ተጉዞ ከወልድያ፣ ጥር 9 ወደ ጎንደር ተጉዞ ከፋሲል ከነማ እንዲሁም ጥር 13 በአዲስ አበባ ስታዲየም ከደደቢት ጋር ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ይታወቃል።

በ2009 ዓ·ም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ወልዲያ አቅንቶ ወልድያን 1–0 ሲያሸንፍ ያሸናፊነቱን ጎል ያስቆጠረው አብዱልከሪም ኒኪማ ነበር። አብዱልከሪም ኒኪማ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2010 ዓ.ም ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ ቀዳሚ ተሰላፊ ከመሆን ጎን ለጎን ከአጥቂ አማካይ ቦታ ላይ እየተነሳ 2 ጎሎችን ለክለቡ ማስቆጠሩ አይዘነጋም፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!

በሚዲያ አጠቃቀም የኋልዮሽ ጉዞ ላይ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ!

በፖለቲካ የተዋጠው፣ የፖለቲከኞች እጅ የተጫነው እግርኳሳችን! - በፈረሰኞቹ ገጽ