የፈረሰኞቹ ገጽ በነገው ዕለት …… !
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ሳምንት ተስተካካይ
ጨዋታውን በመጪው ሐሙስ ምሽት 11 ሰዓት ላይ ያከናውናል፡፡ ይህ በቻን
የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት እና ጨዋታ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረ ጨዋታ ከተደጋጋሚ የጨዋታ ፕሮግራም መቀያየር በኋላ በመጪው ሐሙስ ሊደረግ
ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡
እንደተለመደው ከጨዋታው 1 ቀን አስቀድሞ የፈረሰኞቹ ገጽ ይህንን ጨዋታ ይዳስሳል፡፡ ያሳለፍነው ዓመት
የሁለቱ ክለቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ይመለከታል፡፡ በያዝነው የውድድር ዓመት ሁለቱ ክለቦች ያላቸው ቁጥራዊ ማሳያዎች ይዳሰሳሉ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ ያለው የውጤት ሪከርድን እናቀርባለን፡፡ የድሬዳዋ ከነማ የጨዋታ አቀራረብ እና
የጨዋታ ዘይቤ በፈረሰኞቹ ገጽ ይዳሰሳል፡፡
ይህ የጨዋታ ዳሠሳ እንደተለመደው ሁሉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይቀርባል፡፡ ውድ የፈረሰኞቹ
ገጽ ተከታታዮች፣ እኚህ እና መሰል ከድሬዳዋ ከነማ ጨዋታ ጋር የተያያዙ ዘገባዎችን በነገው ዕለት ከፈረሰኞቹ ገጽ ይጠብቁ!
የፈረሰኞቹ ገጽ!
Comments
Post a Comment