የቅዱስ ጊዮርጊስ የመስመር አጥቂ ተጨዋች ጋዲሳ መብራቴ ጉዳት አስተናገደ!
ጋዲሳ መብራቴ ፈረሰኞቹ ከጅማ አባ ቡና ጨዋታ አስቀድሞ በነበራቸው የመጨረሻ ልምምድ ላይ ጉዳት አስተናግዷል። በዚህ የልምምድ መርኃ ግብር ላይ የተሳተፈው ጋዲሳ የልምምዱ መገባደጃ ላይ የጡንቻ መሸማቀቅ (Hamstring) ጉዳት አስተናግዷል። ተጨዋቹ ይህን ጉዳት ካስተጋናደ በኋላ በስፍራው በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የህክምና እርዳታ ተሰጥቶታል። በመሆኑም ተጨዋቹ ካስተናገደው ጉዳት አንፃር በነገው ዕለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የሚያደርጉት የጨዋታ አካል ይሆናል ተብሎ አይጠበቀም። በዚህም መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነገው ዕለት በጉዳት እና ህመም ምክንያት የማይጠቀማቸው ተጨዋቾች ቁጥር 6 ደርሷል።
Comments
Post a Comment