የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ድንቅ ዝማሬዎች በሚስማር ተራ! Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps - January 01, 2018 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ጋር ተጫውቶ 0-0 በተለያበት ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተለምዶ ሚስማር ተራ በሚባለው ስፍራ የነበራቸው ድንቅ ዝማሬ እና ድጋፍ! Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps Comments
3 የምዕራብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በሙከራ ላይ ይገኛሉ፡፡ - December 26, 2017 ቅዱስ ጊዮርጊስ ለተለያዩ የውጭ አገር ዜግነት ላላቸው ተጨዋቾች የሙከራ ዕድል እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ከተለየዩ ወኪሎች ጋር ግንኙነቶችን በመፍጠር ተጨዋቾች የሙከራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት የተለመደ አሰራር ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሙከራ ጊዜያቸውን በተሳካ መንገድ በማለፍ ለክለቡ የፈረሙ ተጨዋቾች እንዳሉ ሁሉ ቁጥራቸው የበዛ የውጭ አገር ተጨዋቾች በሙከራ ጊዜያቸው አሰልጣኞቹን ማሳመን ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ አገራቸው አሊያም በአገር ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክለቦች እንዳቀኑ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሙከራ ዕድል የሰጣቸው 3 ተጨዋች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተጨዋቾች ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አዲግራት በማቅናቱ ምክንያት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከ20 ዓመት በታች ስብስብ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ከናይጄሪያ፣ ጋና እና ማሊ ሀገራት የመጡ መሆኑን የፈረሰኞቹ ገጽ ምንጮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዛሬው የልምምድ መርኃ ግብር ላይ ተገኝተን መመልከት እንደቻልነው እነዚህ ተጨዋቾች ከዋናው ቡድን ጋር ተቀላቅለው ልምምድ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በቀጣይ ከቡድኑ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ተገምግመው እንዲሁም አሰልጣኞቹን ማሳመን ከቻሉ በ2ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንዲሁም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያ የሚታዩ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው አሰልጣኞቹን ማሳመን ካልቻሉ የሙከራ ጊዜያቸው ማብቃቱን ተከትሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚለያዩ ይሆናል፡፡ Read more
የቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ፡- ወልድያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ - January 11, 2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11 ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ አንስቶ በክልል እና በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዚህ ሳምንት መርኃ ግብሩን የሚያከናውነው በወልድያው ሼህ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ስታዲየም ሲሆን ተጋጣሚው ወልድያ ስፖርት ክለብ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልድያ ስፖርት ክለብ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ አርብ በ 9 ሰዓት ይ ካሄዳል፡፡ ወልድያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፍነው ዓመት እርስ በእርስ ግንኙነት! በ 2009 ዓ . ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ያደረጉት ረቡዕ ጥር 3 ቀን 2009 ዓ . ም ነበር። ይህ ጨዋታ ምሽት 11፡30 የተካሄደ ጨዋታ ሲሆን የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው፡፡ በዚህ ጨዋታ ፈረሰኞቹ ጎል ለማስቆጠር 75 ያህል ደቂቃዎችን ለመጠበቅ ተገደው ነበር፡፡ በጨዋታው 75ኛ ደቂቃ ላይ ሳላሃዲን ሰኢድ የፍጹም ቅጣት ምት መግቢያ ላይ ያገኘውን ኳስ ለአቡበከር ሳኒ ሰጥቶት አቡበከር ሳኒ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጪ መሬት ለመሬት ኳሱን አክርሮ በመምታት የጨዋታውን ብቸኛ ጎል ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ 2009 ዓ . ም የ 2 ኛ ዙር ጨዋታውን ከወልድያ ጋር ያደረገው ረቡዕ ሚያዚያ 18 ቀን 2009 ዓ . ም ነበር፡፡ ይህ ጨዋታ የተካሄደው በወልድያ ስፖርት ክለብ በሼህ መሐመድ አል አሙዲ ስታዲየም ሲሆን የዚህ ጨዋታ ውጤት ለቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አስፈላጊ ውጤት ነበር፡፡ ለዚህም እጅግ በርካታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በ8 አውቶብሶች፣ በግል ትራንስፖርት እና በአየር ወደ ስ Read more
Comments
Post a Comment