የቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ አማካይ ተጨዋች የሆነው ታደለ መንገሻ ልምምድ ጀመረ!
ከወራት በፊት ወደ ህንድ አቅንቶ የጉልበት ቀዶ ህክምና ያደረገው ታደለ መንገሻ ከውድድር ዘመኑ አንስቶ በጉዳት ምክንያት ከፈረሰኞቹ ጋር እንዳልነበር ይታወሳል። ታደለ ባለፉት ወራት የፊዞዮቴራፒ ህክምናን በህክማና ባለሙያዎች እንዲሁም ቀላል የአካል እንቅስቃሴዎችን በጂም ሲያደርግ እንደቆየ መዘገባችንም ይታወሳል።
ይህ የአጥቂ አማካይ ተጨዋች በዛሬው ዕለት በፈረሰኞቹ ልምምድ ላይ መካፈሉን የፈረሰኞቹ ገጽ በልምምድ ሜዳ ተገኝቶ ተመልክቷል። በዕለታዊ ልምምድ ላይ የተገኘው ታደለ መንገሻ ቀላል ልምምዶችን ሲያደርግ ተመልክተነዋል።
ይህ ቀላል ልምምድ ከፈረሰኞቹ ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን አካቷል። ሆኖም ታደለ መንገሻ ከኳስ ጋር የሚደረጉ ልምምዶች ላይ አልተካፈለም፤ በቀጣይ ይህ ተጨዋች ከቀላል ልምምዶች ባሻገር ከኳስ ጋር ወደሚደረጉ ልምምዶች የሚሸጋገር ይሆናል።
Comments
Post a Comment