Posts

Showing posts from January, 2018

የፈረሰኞቹ ገጽ - ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው!

Image
ከአቅማቸው በላይ ሆኖ ወልዲያ፣ ጎንደር እና ወላይታ ሶዶ ላልተጓዙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች «ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው» ብሎ በማለዳ እንደማብሰር ታላቅ ዜና የለም። ያለፉትን ረጅም ቀናት ቅዱስ ጊዮርጊስን ባለማየት ናፍቆት ለተጠጋቸው ደጋፊዎቻችን ይህች ቀን ተናፋቂ ቀን ናት። ይህ የዛሬው ቀን የራሱ ቀለም አለው። የራሱ ቅኝት አለው። የራሱ ስልተ ምት አለው። ቀለሙ ቢጫ፣ ቀይ እና ብርቱካንማ ነው። ቅኝቱ ቅዱስ ጊዮርጊሳዊ ነው። ስልተ ምቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የሚታወቁበት ዝማሬ ነው። ባለፉት ረጅም ቀናት የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ክለቡን ናፍቀዋል ብሎ መግለፅ ስሜታቸው ማሳነስ ነው። ይልቁንም ክለቡን ባለማየት፣ በስታዲየም ባለመታደም፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዝማሬዎች ባለመድመቅ በደረሰባቸው ከባድ ናፍቆት ምክንያት ታመዋል። ይህ ህምም የሚፈወሰው እንደ ዛሬው ባለው ቀን ነው። ይህ ናፍቆት የሚታበሰው የቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያን በሜዳ ውስጥ በማየት ነው። ይህ ናፍቆት የሚሽረው ፈረሰኞቹ በሚጎናፀፉት ድል ነው። የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የስታዲየም ውበት፣ የከተማዋ ድምቀት፣ የኢትዮጽያ እግር ኳስ ህይወት ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ያለው ቀን የአዲስ አበባ ስታዲየምም ሆነ የአዲስ አበባ ዙሪያ ሰላማዊ አየር ይተነፍሳል። እግርኳሳዊ ስሜት እና ጥልቅ የክለብ ፍቅር ብቻ ይነበባል። ይህ ክለብ ለዚህ ዕንቁ ደጋፊ ምኑ እንደሆነ በህይወት እየኖረ ያሳየ የተግባር መምህር፣ የጨዋነት ምሳሌ ነው። ይህ ደጋፊ ከመሪው ክለብ በየትኛውም የነጥብ ርቀት ላይ ቢሆን፣ ቡድኑ በተከታታይ ነጥብ ቢጥል፣ የቡድኑ አቋም ቢዋዥቅ «የመጨረሻዋ ደስታ የኛ ናት» ብሎ አርማውን ከፍ አድርጎ የሚዘምር ደጋፊ ነው። በክለቡ ላይ ከአለት የጠነከረ እምነት በልቡ የያዘ፣

Match Preview:- St George Vs Diredawa Kenema

Image
St George will have its 1st week EPL postponed match tomorrow at 5 ፡ 00pm. It was not played because of preparation for and games of CHAN Africa Cup. The Horsemen will be playing against Diredawa Kenema. St George Vs Diredawa Kenema 2016/17 season meetings! These two teams had their 1st round 2016/17 EPL season clash om Thursday, January 05, 2017. This match was on EPL's 9th week at Addis Ababa stadium at 5 ፡ 30pm. This match was won 3-0 by St George with absolute domination by Adane Girma's 30th min, Salhadin Seid's 67th min and Abdulkareem Nikima's 83rd min goals. The 2nd round match between them in 2016/17 EPL season was played on Saturday, April 20, 2017 at Diredawa stadium at 4:00pm. The Horsemen domination continued and they won 5 to 3. Mehari Mena at the 17th, Adane Girma at the 33rd, Salhadin Seid at 45+1 & 49th, Prince Severniho at the 80th minutes scored to let St George lead by 5-0. But Diredawa Kenema scored 3 g

የቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከነማ

Image
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ3 ተከታታይ የክልል ስታዲየም ጨዋታዎች በኋላ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳል፡፡ ከወልድያ፣ ጎንደር እና ወላይታ ሶዶ ጉዞ እና ጨዋታ በኋላ ከአዲስ አበባ ካሉ ደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ1 ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታውን በነገው ዕለት ምሽት 11 ሰዓት ላይ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ያከናውናል፡፡ ይህ ጨዋታ በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት እና ጨዋታ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረ ጨዋታ እንደሆነ ይታወሳል፡፡  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ ከነማ የ 2009 ዓ.ም የእርስ በእርስ ግንኙነት ! በ 2009 ዓ . ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ያደረጉት ሐሙስ ታህሳስ 27 ቀን 2009 ዓ . ም ነበር። ይህ ጨዋታ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ 9 ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሆኖ የተከናወነ ሲሆን ጨዋታው የተካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ በ 11:30 ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በፍጹም የበላይነት 3 ነጥብ ያገኘበት ጨዋታ ነበር፡፡ በጨዋታው ፈረሰኞቹ 3-0 ያሸነፉ ሲሆን አዳነ ግርማ በ 30 ኛ ደቂቃ፣ ሳላሃዲን ሰኢድ በ 67 ኛ ደቂቃ እና አብዱልከሪም ኒኪማ በ 83 ኛ ደቂቃ ላይ የአሸናፊነት ጎሎችን ማስቆጠራቸው ይታወሳል፡፡ በ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ቡድኖች የ2ኛ ዙር ጨዋታቸውን ያደረጉት ሐሙስ ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ ጨዋታ የተካሄደው በድሬዳዋ ስታዲየም ሲሆን ጨዋታው ጅማሬውን ያደረገው ከቀኑ 10 ሰዓት ሲል ነበር፡፡ በዚህ ጨዋታ ፈረሰኞቹ በመጀመሪያ ዙር የነበራቸውን የበላይነት ያስቀጠሉ