የቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ



የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9 ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ አንስቶ በክልል እና በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዚህ ሳምንት መርኃ ግብሩን የሚያከናውነው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲሆን ተጋጣሚው መከላከያ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ቅዳሜ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ያሳለፍነው ዓመት የእርስ በእርስ ግንኙነት!

2009 . የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ያደረጉት እሁድ ህዳር 18 ቀን 2009 . ነበር። ይህ ጨዋታ 2009 . የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3 ሳምንት መርኃ ግብር ሆኖ የተከናወነ ሲሆን ጨዋታው የተካሄደው ምሽት 1130 ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ዘንድ የሚታወስ ጨዋታ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ፈረሰኞቹ ጨዋታው በተጀመረ 37 ደቂቃ ላይ መሃሪ መናን በቀይ ካርድ ከሜዳ ያጣሉ፡፡ 

የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜም 0-0 በሆነ ውጤት ተጠናቆ ተጨዋቾቹ ወደ መልበሻ ቤት ያቀናሉ፡፡ በጨዋታው 2 አጋማሽ የተከሰተው ግን እጅግ አስገራሚ ነገር ነበር፡፡ 1 ተጨዋች በቀይ ካርድ ያጡት ፈረሰኞቹ በአስገራሚ ተነሳሽነት እና የማሸነፍ ወኔ ወደ ሜዳ ተመለሱ፡፡ ጨዋታውን ተቆጣጠሩ፡፡ በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚያቸው የሜዳ ክፍል ይደርሱ ጀመር፡፡ 

አብዱልከሪም ኒኪማ ከአበባው ቡጣቆ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ቀዳሚውን ጎል አስቆጠረ፡፡ አዳነ ግርማ በድጋሚ ከአበባው ቡጣቆ የደረሰውን ኳስ ተጠቅሞ ቡድኑን 2-0 እንዲመራ አስቻለ፡፡ በመጨረሻ ሳላሃዲን ሰኢድ 3 ጎል አስቆጥሮ ፈረሰኞቹ በጎዶሎ ልጅ መከላከያን 3-0 ማሸነፍ ቻሉ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2009 ዓ.ም የ2ኛ ዙር ጨዋታውን ከመከላከያ ጋር ያደረገው አርብ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ.ም ነበር፡፡ ይህ ጨዋታ በተስተካካይ የጨዋታ መርኃ ግብር የተካሄደ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18 ሳምንት መርኃ ግብር ላይ ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያደርገው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ምክንያት ፈረሰኞቹ ሳያካሄ ከቀሩት 2 ተስተካካይ ጨዋታዎች መካከል አንደኛው ጨዋታ ሆኖ በዕለተ አርብ ተከናውኗል፡፡ እንዲሁም አሰልጣኝ ማርት ኖይ በቤተሰብ ችግር ምክንያት ወደ ትውልድ አገራቸው በማቅናታቸው ምክንያት ይህ ጨዋታ የተመራው በምክትል አሰልጣኞቹ ፋሲል ተካልኝ እና ዘሪሁን ሸንገታ ነበር፡፡

የዚህ ጨዋታ አሸናፊ መሆን የቻለው መከላከያ ነው፡፡ መከላከያ ከኋላ በመነሳት ጨዋታውን 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ በጨዋታው 52ኛ ደቂቃ ላይ አቡዱልከሪም ኒኪማ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ እና ኳሱን ከመስመር ወደ መሃል እያጠበበ በመግፋት የመከላከያ ተጨዋቾችን አታሎ ያስቆጠረው ጎል ፈረሰኞቹን ቀዳሚ ቢያደርጋቸውም መከላከያዎች በ59 እኛ በ63ኛ ደቂቃ ላይ ባስቆጠሩት ጎል ታግዘው ፈረሰኞቹን 2-1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ 


የዘንድሮ የውድድር ዓመት ቁጥሮች ስለ ሁለቱ ቡድኖች ምን ያሳያሉ?

ቅዱስ ጊዮርጊስ በያዝነው የውድድር አመት 6 ጨዋታዎችን ሲያደርግ 3 ጨዋታዎችን በአሸናፊነት ተወጥቶ የተቀረውን 3 ጨዋታ በአቻ ውጤት ፈጽሟል፡፡ መከላከያ በበኩሉ ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች መካከል 2 ጨዋታን በአሸናፊነት፣ 3 ጨዋታን በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ 3 ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ በዚህ ውጤት መሰረት ፈረሰኞቹ 12 ነጥብ በመሰብሰብ በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ 2 ደረጃ ላይ ሲገኙ፣ መከላከያ 9 ነጥቦችን በመያዝ 10 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡


መከላከያ በያዝነው የውድድር ዓመት በአዲስ አበባ ስታዲየም 6 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ በእነዚህ 6 ጨዋታዎች ላይ 1ጨዋታን ማሸነፍ ሲችል፣ 2 ጨዋታ ሽንፈትን አስተናግዶ የተቀሩትን 3 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማሸነፍ የቻለው ድሬዳዋ ከነማን ሲሆን ጨዋታው የተጠናቀቀው 1-0 በሆነ ውጤት ነው፡፡ ይህ ክለብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሽንፈትን ያስተናገደው በወላይታ ድቻ እና በኢትዮጵያ ቡና ሲሆን ጨዋታው የተጠናቀቀው በተመሳሳይ 1-0 በሆነ ውጤት ነው፡፡ መከላከያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ካደረጋቸው 6 ጨዋታዎች መካከል በ3 ጨዋታዎች አቻ ሲያጠናቅቅ ክለቦቹ ኢትዮ. ኤሌክትሪክ፣ አዳማ ከነማ እና ሀዋሳ ከነማ ናቸው፡፡ ከኢትዮ ኤሉክትሪክ 1-1፣ ከአዳማ ከነማ 0-0 እንዲሁም ከሃዋሳ ከነማ 1-1 የአቻ ውጤቶቹ ናቸው፡፡  መከላከያ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች ላይ 3 ጎሎችን ሲያስቆጥር 4 ጎሎችን አስተናግዷል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ የሆነው መከላከያ በያዝነው የውድድር ዓመት ከሜዳው ውጪ ያደረገው 2 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ነው፡፡ ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ማድረግ ከቻሉት 2 ጨዋታዎች መካከል በአንድ ጨዋታ ድል ሲቀናቸው በቀሪው አንድ ጨዋታ ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡ መከላከያዎች ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው የተጫወቱት ከአርባምንጭ ከነማ እና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሲሆን ወደ አርባምንጭ አቅንተው በአርባምንጭ 2-0 ሲሸነፉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት 1-0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ መከላከያ በአጠቃላይ ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ 1 ጎል ሲያስቆጥር 2 ጎሎችን አስተናግዷል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረጋቸው 6 ጨዋታዎች 8 ጎሎችን ሲያስቆጥር 2 ጎሎቹን አስተናግዷል፡፡ መከላከያ በበኩሉ 8 ጨዋታዎች 4 ጎሎችን ሲያስቆጥር 6 ጎሎችን አስተናግዷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአማካይ በጨዋታ 1.33 ጎሎችን ሲያስቆጥሩ መከላከያ በጨዋታ በአማካይ 0.5 ጎል እያስቆጠሩ ለዚህ ጨዋታ ደርሰዋል፡፡ በመከላከል ረገድ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጨዋታ በአማካይ 0.33 ጎሎችን ሲያስተናግድ መከላከያ በጨዋታ በአማካይ 0.75 ጎል አስተናግዷል፡፡


የመከላከያ የጨዋታ አቀራረብ!

የአሰልጣኝ ምንያምር ፀጋዬ መከላከያ በሊጉ ጅማሬ ላይ የውጤት ማጣት ላይ ቢቆይም ያለፉትን 2 ጨዋታዎች ማሸነፍ በመቻሉ ወደ ውጤታማነት በመመለስ ላይ የሚገኝ ስብስብ ነው፡፡ አሰልጣኙ በያዝነው የውድድር ዓመት 4-4-2 እና 4-2-3-1 የጨዋታ ዘይቤን ለመተግበር ሲንቀሳቀሱ ተመልክተናል፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ባደረጓቸው በርካታ ጨዋታዎች ላይ 4-4-2 የጨዋታ ዘይቤ ላይ ምርጫቸውን ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ድሬዳዋ ከነማ ላይ መከላከያዎች 4-4-2 የጨዋታ ፎርሜሽንን ለመተግበር ተንቀሳቅሰዋል፡፡ መከላከያ ከጉዳት፣ ከብሔራዊ ቡድን ተልዕኮ እና ከብቃት በተያየዘ ውስን ተጨዋቾችን ለዋውጦ ለመጠቀም ቢሞክርም በአንፃራዊነት በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የሚገቡ ተጨዋቾች የሚታወቁበት ክለብ ነው፡፡

በ4-4-2 የጨዋታ ፎርሜሽን የፊት አጥቂነትን በዘላቂነት መያዝ የቻለው ምንይሉ ወንድሙ ለመከላከያ ጥንካሬ የሚጠቀስ ተጨዋች ነው፡፡ ይህ ተጨዋች መከላከያ ባለፉት 3 ጨዋታዎች ማሳካት ለቻሉት 7 ነጥብ ተጠቃሽ ተጨዋች ነው፡፡ ምንይሉ ባለፉት 3 ጨዋታዎች ላይ 3 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

መከላከያ በ4-4-2 ፎርሜሽን ውስጥ እጅግ ደካማ ጎኑ በቡድኑ የአማካይ ክፍል እና የአጥቂ ክፍል መካከል ያለው ርቀት ነው፡፡ 4ቱ የመከላከያ አማካዮች በአንጻራዊነት ከፊት አጥቂዎቹ የራቁ ናቸው፡፡ ቡድኑ ኳስ ይዞ ለመጫወት ፍላጎት እንዳለው ቢታይም በተጨዋች መካከል ባለው የቦታ አጠቃቀም ችግር ምክንያት ይህ ፍላጎታቸው እንቅፋት ሲገጥመው ይታያል፡፡ በዚህ ጫና ምክንያት የቡድኑ የፊት አጥቂዎች ከሌላው ቡድን በተደጋጋሚ ይነጠላሉ፡፡ ይህም በጨዋታዎች ላይ በተደጋጋሚ ይታያል፡፡ በዚህ ጫና ውስጥ የሚወድቁት የፊት አጥቂዎቹ ወደ ጨዋታ ራሳቸውን ለመመለስ ወደ መስመር በመውጣት ራሳቸውን ለመልሶ ማጥቃት ሲያዘጋጁ ይታያሉ፡፡

 መከላከያ በመሃል ሜዳ በሚጠቀማቸው 4 ተጨዋቾች ምክንያት በተጋጣሚ ቡድን በቁጥር የመበለጥ እውነታ ሲገጥመው አይተናል፡፡ በተለይም ተጋጣሚ ቡድን 4-3-3 እና 4-2-3-1 የጨዋታ ዘይቤን ሲተገብር በመሃል ሜዳ ያለው የተጨዋቾች ቁጥር 3ለ2 ሲሆን ይታያል፡፡ በዚህም የመከላከያ ተጨዋቾች በ1 ተጨዋች መበለጥ ሲገጥማቸው በመፍትሄነት የሚጠቀሙት ሜዳውን በማጥበብ የመስመር አማካዮችን ወደ መሃል ሜዳ በማስገባት የቁጥር ልዩነቱን ለማስተካከል ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ይታያሉ፡፡

 

በፈረሰኞቹ ቤት በጉዳት የማይሰለፉ ተጨዋቾች!

ከጉዳት ጋር ተያይዞ አሜ መሃመድ፣ ሳላሃዲን ሰኢድ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና ታደለ መንገሻ ከጉዳታቸው ማገገም ባለመቻላቸው የዚህ ጨዋታ አካል አይሆኑም፡፡ ከዚህ ውጪ በፈረሰኞቹ ቤት አዲስ ጉዳት የለም፡፡

እናሸንፋለን፣
በሳንጃው ሙሉ እምነት አለን!


Comments

Popular posts from this blog

3 የምዕራብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው ተጨዋቾች በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በሙከራ ላይ ይገኛሉ፡፡

የቅድመ ጨዋታ ዳሠሳ፡- ወልድያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ

ጅማ - ደማችን የፈሰሰባት፣ ድላችንን የተቀማንባት ከተማ!