ትውስታ - በ2017 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጉዞ - ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)
የ2018 የቶታል ካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የክለቦች ውድድር በያዝነው ሳምንት መገባደጃ ላይ ይጀመራል፡፡ በዚህ ውድድር ለተከታታይ 4 አመታት ኢትዮጵያን በመወከል ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ይሳተፋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ የክለቦች ታሪክ በአፍሪካ ሻምዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ውስጥ የገባ የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ክለብ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም የዘንድሮው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ መጀመርን ተንተርሰን ያሳለፍነው ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጉዞን እያነሳሳን እንገኛለን፡፡ ባለፉት ቀናት በክፍል አንድ እና ሁለት ምልከታችን ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2017 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ፣ የ1ኛ ዙር እና የምድቡ የመጀመሪያ 3 ጨዋታዎችን ማነሳሳታችን ይታወሳል፡፡ ለዛሬ በክፍል 3 እና በመጨረሻ ክፍል ያዘጋጀነው ጽሑፍ ይህንን ይመስላል፡፡ ኤኤስ ቪታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይህ ጨዋታ የ2017 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ 4ኛ ጨዋታ ሆኖ ተከናውኗል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስከዚህ ጨዋታ ድረስ 9 ጎል አስቆጥሮ ምንም ጎል አላስተናገደም፡፡ የተጋጣሚዎቹን መረብ 9 ጊዜ ጎብኝቶ የራሱን መረብ በሚገባ ከጥቃት ጠብቆ ቆይቷል፡፡ ከታላላቆቹ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ ጋር ጨዋታውን አድርጎ ጎሉን አላስደፈረም፡፡ በዚህም የተከላካይ ክፍሉ ጥንካሬ በግልጽ ታይቷል፡፡ የመሃል ተከላካዮቹን አስቻለው ታመነን እና ሳላሃዲን በርጌቾን በምርጥ 11 የካፍ ስብስብ ውስጥ አስገብቷል፡፡ በሌላ በኩል አሰልጣኝ ማርት ኖይ ወደ ክለቡ እንደማይመለሱ እርግጥ ሆኗል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ስብሰባ አድርገው ምክትል አስልጣኞቹ ፋሲል ተካልኝ እና ዘሪሁን ሽንገታ ክለቡን ይዘው እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ በዚህም ፈረሰኞቹ በምክትል አሰልጣኞቹ እየተመሩ ወደ...


Comments
Post a Comment