የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ 12 ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ተስተካካይ ጨዋታ በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የ12ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ መርኃ ግብሮችን በማስተላለፉ ምክንያት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ይታወቃል፡፡ ይህ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በደደቢት መካከል የሚካሄደው ጨዋታ ነገ ( እሁድ ) በ 10 ሰዓት ጅማሮውን ያደርጋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት የ 2009 ዓ . ም የእርስ በእርስ ግንኙነት ! በ 2009 ዓ . ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ያደረጉት እሁድ ህዳር 11 ቀን 2009 ዓ . ም ነበር። ይህ ጨዋታ የ 2009 ዓ . ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ 2 ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሆኖ የተከናወነ ሲሆን ፈረሰኞቹ 2–0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል። በዚህ ጨዋታ የፈረሰኞቹን ቀዳሚ ጎል ያስቆጠረው ምንተስኖት አዳነ በ 23 ኛው ደቂቃ ላይ ነበር፡፡ በ 23 ተኛ ደቂቃ በሃይሉ አሰፋ ከግራ ጥላ ፎቅ አቅራቢያ ያሻገረው ኳስ ናትናኤል ዘለቀ በግንባር ሲገጨው በድጋሚ ምንተስኖት አግኝቶት ኳስን በግንባር ገጭቶ ቀዳሚውን ጎል አስቆጥሯል፡፡ እንዲሁም በ 45 ኛ ደቂቃ በድጋሚ በሃይሉ አሰፋ ከማዕዘን ምት ያሻገረው ኳስ አዳነ ግርማ 2 ኛውን ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በፈረሰኞቹ 2-0 እንዲጠናቀቅ ሆኗል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የ 2009 ዓ . ም የ 2 ኛ ዙር ጨዋታውን ከደደቢት ጋር ያደረገው ቅዳሜ የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ .